ሒስኑል ሙስሊም

2.00 $

በሙስሊሙ ዓለም እጅግ ተወዳጅና በብዛት ተሠራጭተው ካሉ ትናንሽ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዚክር (አላህን ማውሳት እና ማወደስ) አንድ ሙስሊም ራሱን ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ የሚጠብቅበት፤ የተመኘዉንም ነገር የሚያሳካበት ምሽጉ ነው፡፡ ይህች አነስተኛ መጽሐፍ አንድ ሙስሊም ከንጋት እስከ ምሽት ባለው ጊዜ ዉስጥ ሊያደርጋቸው የሚገቡ የተለያዩ የዕለት ተዕለት ዉዳሴዎችን ይዛለች፡፡ 131 የዚክር ዓይነቶች የተካተቱበት ይህ መጽሐፍ ከምንጩ ቋንቋ ዐረብኛ የቃል በቃል ትርጉም ወደ አማርኛ የተመለሰ ሲሆን አስፈላጊ ማብራሪያዎች ተካተውበታል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሰዒድ ኢብኑ ዐሊ ወህፍ አል ቀሕጧኒ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 255
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 1997
ከመጽሐፉ ፡ ከዚክር ትሩፋት ፡ ዐብደላህ ኢብኑ ቡስር እንዳስተላለፉት አንድ ግለሰብ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) መጣና የኢስላም ህግጋት በጣም በዝተዉብኛል፤ በርሱ የምፀናበትን አንዳች ነገር ይንገሩኝ፡፡” አላቸው፡፡ እርሣቸዉም “ ምላስህ አላህን በማውሳት የረጠበ ከመሆን አይቆጠብ ፡፡” አሉት፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት