Weight | 135 g |
---|
ሐያቱ ታቢኢን ቁጥር አንድ
3.00 $
ታቢዒዪኖች የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች ተከትለው የመጡ ከነርሱ ጋር የተገናኙና የኖሩ ትውልዶች፡፡ ይህ መጽሐፍ በሁለት ቅጽ የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ታቦዒዮችን የሕይወት ታሪክ (ሐያቱ ታቢዒን) አጠር ባለ መልኩ ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉን ያዘጋጁት ሐያቱ ሶሐባን ያዘጋጁት ዶ/ር ዐብዱራሕማን ረእፈት አልባሻ ናቸው፡፡ የታቢዒ ትውልዶች ዘመናቸውን ወርቃማ በማድረግ ዓለምን በበጐ ሥራዎቻቸውና በዕውቀታቸው ያደመቁ ነበሩ፡፡ ኢስላም በኢስያ አህጉር ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ከፀሐይ መውጪያ እስከ ፀሐይ መግቢያ እንዲስፋፋ ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡ የአባቶቻቸውን ዓላማ ክንዳቸውን እስኪንተራሱ ከግቡ አድርሰዋል፡፡ መጽሐፉ ይህንን ይነግረናል፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብዱረሕማን ረእፈት አልባሻ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ ቁጥር አንድ ፤ 145 ገፆች ቁጥር ሁለት ፡ 119 ገፆች
የታተመበት ዓመት ፡ ቁጥር አንድ ፡ ነሐሴ 1999 ቁጥር ሁለት ፡ ጥቅምት 2003
ከመጽሐፉ፡ በቁጥር አንድ መጽሐፍ ዉስጥ የዐጧእ ኢብኑ አቢ ረባሕ፤ ዓሚር ኢብኑ ዐብዱላህ አት-ተሚሚ፣ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር፣ ረቢዕ ኢብኑ ኹሠይም፣ ኢያስ ኢብኑ ሙዓዊያ ፣ ዑመር ዐብዱልዐዚዝ፣ ሐሰን አልበስሪ፣ ሹረይሕ አል-ቃዲ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን፣ ረቢዐቱ ረእይ፣ ረጃእ ኢብኑ ሐይወት፣ ሸዕቢ፣ ሰለመት ኢብኑ ዲናር፣ ሰዒብ ኢብኑ ሙሰየብ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ዋሲዕ ታሪኮችን ያገኛሉ፡፡
በቁጥር ሁለት – የሙሐመድ ኢብኑ አልሐነፊያ፣ ጧዉስ ኢብኑ ከይሳን፣ ቃሲም ኢብኑ ሙሐመድ፣ ሲለት ኢብኑ አሽየም፣ ዘይኑል ዓቢዲን፣ አቡ ሙስሊም አል-ኸውላኒ፣ ሳሊም ኢብኑ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣ ዐብዱረሕማን አልጋፊቂ፣ ነጃሺ፣ ሩፈይዕ ኢብኑ ሚህራን፣ አሕነፍ ኢብኑ ቀይስ፣ አቡ ሐኒፋ ታሪኮችን ያገኛል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት