ሐያቱ ሶሓባ ስስ ከቨር

9.00 $

ከኢስላማዊው የእውቀት ማዕከል በቂ ኩትኮታና ስልጠና የተሰጣቸውየኢስላም የበኩር ልጆች፣ የመጀመሪያው ትውልድ ዕንቁ አባላት የነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ባልደረቦች (ሶሐቦች)፤ በመልካም ሥነ-ምግባራቸው፣ ባማረ ማኅበራዊ ውሏቸው፣ በታጋሽነት፣ ትህትና፣ በለጋስነትና ሌሎችም ድንቅ ሰብዓዊ ባሕሪያት ከነርሱ በኋላ ላሉ ትውልዶች በሙሉ በመልካም አርአያነት ዝንተ ዓለም ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡
ይህ መጽሐፍ በዚሁ ዙርያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፃፉ እጅግ ተነባቢ እና ተወዳጅ ከሆኑ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በአንድ ቅጽ ከ100 በላይ የሆኑ ሶሐቦችን አጭር የሕይወት ታሪካቸዉን ይዞ  የተሰናዳ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብዱረሕማን ረእፈት አልባሻ
ትርጉም ፡ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 623
የታተመበት ዓመት ፡ 2011
ከመጽሐፉ ፡
ታላቁ ሶሐባ ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ የሶሐቦችን ገድል በዘከሩበት ንግግራቸው እንዲህ ይሉናል፡-
“አርአያ ሊሆነው የሚችል ስብዕና የሚሻ ካለ የመልዕክተኛው ባልደረቦች ብቻ ናቸው አርአያ ሊሆኑት የሚችሉት -የሶሐባ ትውልድ አባላት፡፡ ምክንያቱም እነሱ ከማንም በላቀ ሁናቴ የጻዕድ ልቦናና የጠለቀ ዕውቀት ባለሀብቶች ነበሩና፡፡ ቀላልና የተረጋጋ ሕይወት መርተዋል፡፡ ቀጥተኛውን ጐዳና ተከትለዋል፡፡ ከየትኛውም ትውልድ ይልቅ በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኙ ነበር፡፡ አላህ ለመልዕክተኛው ባልደረባነት አጭቷቸዋል፡፡ የዚህን ዲን ታላቅ አደራ አሸክሟቸዋል፡፡ ማንነታቸውን እወቁ፤ ፈለጋቸውንም ተከተሉ፤ ቀጥተኛውን የሕይወት ፈር የተከተሉ ሰዎች ነበሩና፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: