ሐያቱ ሶሐባ ቅጽ አንድ

3.00 $

“ሱወሩን ሚን ሐያቲ ሶሐባ” /የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ባልደረቦች አጭር የህይወት ታሪክ/ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተነባቢ እና ተወዳጅ መጽሐፍ ነው፡፡ የነዚያን የምርጥ ትውልዶችን የነቢዩን ባልደረቦች ታሪክ ባማረ ሥነጽሑፍ እና ትርጉም ያስዳስሰናል፡፡ መጽሐፉ በአራት ቅፆች የተከፋፈለ ሲሆን በያንዳንዱ ቅጽም የተለያዩ ሶሖቦችን ታሪክ ያስዳስሰናል፡፡ በመጽሐፉ ዉስጥ የሶሐቦችን የሥነ-ምግባር ምጥቀት የዕውቀት ሥፋት የዓላማ ጽናት እንዲሁም መልካም ስብዕና ከታላላቅ ኢስላማዊ ገድሎቻቸው ጋር እናነባለን፡፡
በዚህ ቅጽ የዐብደላ ኢብኑ ዐባስ፣ የዐብደላ ኢብኑ ሑዛፋ፣ የዐብደላ ኢብኑ ጀሕሽ፣ የዐብደላ ኢብኑ መስዑድ፣ የዐብደላ ኢብኑ ሰላም፣ የዐብደላ ኢብኑ ዑመር፣ የዐብደላ ኢብኑ ኡሚ መክቱም፣ የዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ፣ አቡ አዩብ አልአንሷሪ፣ የአቡ ዘር አልጊፋሪ፣ የአቡ ሁረይራ፣ ሰልማን አልፋሪሲ፣ ሱሀይብ አልሩሚ፣ ጁለይቢብ፣ ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ፣ ዑመይር ኢብኑ ሰዕድ፣ ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ጦልሓ ኢብኑ ዑበይዱላህ፣ ዑቅበት ኢብኑ ዓሚር፣ ኸባብ ኢብኑ አልአረት፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪ፣ አቡ ሱፍያን፣ የአቡ ደርዳእ፣ የበረካ፣ የረምላ ቢንት አቢ ሱፍያን፣ የሑዘይፋ ኢብኑል የማን፣ የአስማእ፣ የፋጢማ፣ የኡሙ ሱለይም፣ የኡሙ ሐኪም፣ የኡሙ ዐማራ፣ የኡሙ ሐቢባ፣ የኡሙ ሰለመህ፣ አስማእ ቢንት ዑመይስ፣ ፋጢማ ቢንት አሰድ፣ የዓኢሻ፣ የኡሙ ኩልሡም፣ የሩቀያ፣ የሱመያ፣ የሶፊያ ታሪኮችን
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብዱረሕማን ረእፈት አልባሻ
ትርጉም ፡ ዶ/ር ኢድሪስ መሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 254
የታተመበት ዓመት ፡ ህዳር 1988

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: