Weight | 222 g |
---|
ሐላልን ፍለጋ
6.00 $
በተለይ በዚህ ባለንበት ዓለም ተጨባጭ ኢስላማዊ ልብ ወለድ አፃፃፍ እስልምናን ለማስተማር ሌላኛው የዳዕዋ መንገድ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ መጽሐፍ በነጃሺ ሲታተም በዓይነቱ የመጀመርያው ነው መላት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የካምፓስን ሕይወት ዉሎ አዳርና የሐላል ጥምረት ፍለጋ ጉዞን ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉ ከእስልምና አስተምህሮ ባልወጣ መልኩ፣ አደብ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ፣ ቀጥተኛና ማራኪ በሆነ አገላለጽ የተዘጋጀ ነው፡፡ ወጣቶችም ሆነ ሌሎች ቢያነቡት ትምህርት ያገኙበታል፡፡
ዝግጅት : ሰይድ ሺፈራው
የገጽ ብዛት ፡ 247
የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ከመጽሐፉ ፡ ፈንጠር ብሎ ቆመና የቂርኣኑን ባለቤት ይጠብቅ ጀመር፡፡ በሀሳብ ግን ስምጥ ብሎ ሄዷል፡፡
‘‘የቁርኣን ክብር ይሄ ነው እንዴ? የአላህ ቃል ልቅና የት ገባ? እንደ ቀድሞው
ትውልድ ማክበር እንደሚገባን ምነው ዘነጋን? የቁርኣንን ተዓምር አቅላችንን ምን አሳጣው? ማማራችንስ መከበራችንስ በሱው አልነበረም እንዴ? ምን ነካን?’’
‘‘ዳዒዎቻችንስ ስለ ቁርኣን ክብር ጉዳይ በሰፊው ለምን አይሰብኩም? እነሱ ትኩረት በደንብ ካልሰጡት ቁርአኑን በግራ እጁ ይዞ እግር ኳስ የሚጫወተውን ማን ይመልሰው?’’
ሰሐቦች ቁርኣንን ሲይዙ ለአላህ ካላቸው ፍቅር የተነሳ እያለቀሱ ‘‘ይህ የጌታችን ቃል ነው!’’ ይሉ ነበር የሚለውን ታሪክ ያነበበትን መጽሀፍ አስታወሰ፡፡
ወደ ቁርኣኑ አንዲት ሴት ስትሄድ ተመልክቶ ከሀሳቡ ተመልሶ እሱም ወደዚያው አመራ፡፡ ……
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት