ሐላልና ሐራም ቁጥር 1

4.00 $

በኢስላም በተፈቀዱ እና ባልተፈቀዱ ነገሮች ዙርያ የአንድን ሙስሊም ግላዊ ሕይወት የሚመለከቱ ጉዳዮች፣ አጠቃላይ ህይወት እምነቶችና ባህሎች፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች፣ ስለ ጋብቻና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች፣ ስለ ወሊድ ቁጥጥር፣ የተጋቢዎች የግንኙነት መብቶች፣ ስለ ወላጆችና ልጆች፣ ስለ መዝናኛ፣ ሙስሊም ከላሆኑ ሰዎች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት እና ሌሎችም በጥልቀትና በምጥቀት የተዳሰሱበት ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አዘጋጁ ዓለም አቀፍ እውቅ ሙስሊም ዳዒ ናቸው፡፡ በ1960 እ.ኤ.አ የጻፉት ይህ መጽሐፋቸው በዐረቡ ዓለም በሚሊዮን ቅጂዎች ተሽጧል፡፡ ከ28 ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ታትሟል፡፡ መጽሐፈ አንድ ሙስሊም ሐላልና ሐራም የሆኑ ነገሮችን ለይቶ እንዲያውቅ ይረዳል፡፡
መጽሐፉ በሦስት ቅጽ (ቅጽ አንድ፣ ሁለት እና ሦስት) የተዘጋጀ ነው፡፡
ቁጥር አንድ 121 ገፆች ያሉት ሲሆን
ቁጥር ሁለት በ129 ገፆች
ቁጥር ሦስት ደግሞ በ 128ገፆች የተሰናዳ ነው፡፡
አዘጋጅ፡ ፕ/ር ሸይኽ ዩሱፍ አልቀረዷዊ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
የታተመበት ዓመት ፡ 1998/99
ከመጽሐፉ ፡ የሰዉን ገንዘብ በግልጽም በስዉርም ያለአግባብ መንካት ሐራም እንደሆነው ሁሉ የራስ ገንዘብም ክብር አለው፡፡ ባለቤቱ እንዲያጠፋው እንዲያባክነው፣ እንደሻው እንዲበትነው አይፈቀድለትም፡፡ ምክንያቱም መኅበረሰቡ ከግለሰቦች ገንዘብ የባለቤትነት ድርሻ አለው፡፡

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

 

Category: