ልብ ላላሉ ልቦች

3.00 $

መጽሐፉ አኺራን የሚያስታውሱ ቀልብን የሚያለሰልሱ በተለያዩ ሥነልቦናዊ፣ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሥነምግባራዊ  ጉዳዮች ዙርያ ያተኮሩ ምርጥ መጣጥፎች የተካተቱበት ነው፡፡በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ አዝናኝ፣ አስተዋሽና አስተማሪ የሆኑ አጫጭር ምክሮችና መልዕክቶች የተካተቱበት
አዘጋጅ – ሙሐመድ ሰዒድ
የገፅ ብዛት ፡ 104
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2005
ከመጽሐፉ ፡
ቀኑ ሰዓቱን ጠብቆ ይመሻል፤ ምሽቱም ተረኛ መሆኑን አውቆ ከተፍ ይላል፤ ክረምት ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፤ በጋም በእግሩ ይተካል፤ ሁሉም ተራ ቀጠሮውን ያውቃል፤ በተሠጠው የጊዜ ሠሌዳ ይመራል፤የተሰጠውንም ቆይታ ጨርሶ ይሄዳል፡፡ ፀሐይና ምድር የራሳቸው የሆነ ምህዋር አላቸው፤ ክዋክብት ጨረቃም እንዲሁ – ሳይጋጩ ይጓዛሉ፤ ሣይላተሙም ከየማረፊያቸው ይደርሳሉ፡፡ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተል፤ ፍሰታቸውን የሚቆጣጠር፤ ሒደታቸዉን የሚያስተናብር፤ ቅንጅታቸውን የሚያሠካካ .. አንድ ኃይል ያለ ይመስላል፡፡ ይህ ሁሉ ለሚያስተነትን ሰው ምልክት ነው፡፡ አርቆ ለሚያይም ትምህርት ነው ፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: