Additional information
Weight | 1090 g |
---|
17.00 $
ከኢስላም በፊት ከተፈጸሙ ታሪካዊ ክስተቶች ጀምሮ የመልእክተኛውን የሕይወት ታሪክ በሙሉ የዳሰሰው ለዓለማት እዝነት የተሰኘው መጽሐፍ በውስጡ ዳጎስ ያሉ ታሪኮችንና ከውስጡ የሚገኙትን አስተምህሮቶች ጨምሮ ይዟል፡፡ በቅድመ እስልምና የነበሩ ሥልጣኔዎች ምንነት፣ በቀደመው የአረብ ህዝቦችና የዘር ግንድና ሥልጣኔያቸውን በስፋት ተዳሷል፡፡ የታላቁ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከልጅነት እስከ ነብይነት፣ የወህይ መውረድ፣ የድብቅና ግልጽ የጥሪ ሂደት ካሳለፉት የዳዕዋ ሕይወት በርካታ ትምህርቶች ቀርበዋል፡፡መልእክተኛው (ሰዐወ) በዳዕዋ ሕይወታቸው የገጠማቸው ውጣ ውረድ መከራዎች ከመካ አጋሪዎች የተጋረጠባቸውን ፈተና፤ ወደ ሐበሻ ያደረጉትን ስደትና የገጠማቸው ብርቱ የሐዘን አመት እያወሳ በዘመናችን ችግሮችን እንዴት እንደምንጋፈጥ ያስተምረናል፡፡በዳዕዋ ሕይወታቸው ያደረጉትን ትግል የተገቡላቸውን ቃልኪዳን፣ ወደ መካ ያደረጉትን ስደት፤ በመዲና ስለገነቡት መንግሥትና ያሳለፉትን ጣፋጭ ሕይወት ከነ ሙሉ ታሪኩና አስተምህሮቱ እንድንማርበት ተተርኮ ቀርቧል፡፡ ስለ መዲናው ህገመንግስት ፣ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዴት እንደኖሩ፣ ስለሙሃጂሮችና አንሳር ግንኙነቶች፣ እንዲሁም በዘመናቸው ስለ ተደረጉ ዘመቻዎች በልዩ አቀራር ይተነተንበታል፡፡
የመጽሐፉ ርዕስ፡ ለዓለማት እዝነት
አዘጋጅ፡ ዶክተር ዐሊ ሙሐመድ አስ ሶልላቢ
ትርጉም፡ አሕመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት፡928
Weight | 1090 g |
---|