ለምን ተፈጠርን?

1.00 $

ይህ መጽሐፍ ስለ ፍጥረተ ዓለሙ ፈጣሪ ሕይውነት አመላካች የሆኑ ነገሮችን በመዘርዘር ለኢ-አማንያን ምላሽ የሚሆኑ ማስረጃዎችን ከቁርኣን እያጣቀሰ ይተነትናል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የሰውን ልጅ የመፈጠሩ ዓለማ ለምንታን (ለምን-ተፈጠረ) ለማስረዳት በርካታ ማሳያዎችን ያስቀምጣል፡፡ በርግጥም የሰው ልጅ ማን እንደፈጠረውና ለምን ዓላማ እንደተፈጠረ ሊያውቅ ይገባል፡፡ ፈላስፎች በየጊዜው ከየራሳቸው ግምት ተነስተው ሰውን ወደ ተቀበዣዠረ አመለካከት ሲከቱት ቆይተዋል ቁስ አካላውያን “የሰው ልጅ እዚህ ምድር ላይ ለመገኘቱ ዓላማ የለውም” የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ አዘጋጁና ዕውቁ ዳዒ በዚህ መጽፋው ከዚህና ከሌሎችም የዓለማውያን ቅብጥርጥር ተነስቶ አላህ የሰውን ልጅ ለምን እንደፈጠረ ግልጽ አድርጐ ያሳዩበት መጽሐፍ ነው፡፡
ዝግጅት ፡ አቡ አሚና ቢላል ፊሊፕስ
ትርጉም ፡ አብይ ጣሰው
የገጽ ብዛት ፡ 56
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2002
ከመጽሐፉ፡ እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በሕይወቱ አንድ ጊዜ “ለምን ተፈጠርኩ ?” ወይም “ለምን ጉዳይ በዚህ ምድር ላይ ተገኘሁ ?” ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ የመፈጠር ዓላም የሰው ልጅ በሕይወቱ እስካለ ድረስ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡ የሥራ መኖር ሠሪ እንዳለ እንደሚያመለክተው ሁሉ የዚህ ፍጥረተ ዓለምና የሰው ልጅ ዉስብስብ አወቃቀር አንድ ኃያል ፈጣሪ እንዳለ ያመለክታሉ፡፡ …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: