ህልም አለኝ

5.00 $

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ቁርኣንና ሐዲሥን መሠረት አድርገው የተፃፉ ሀሳቦችና መልዕክቶች በተለያየ ከ30 በላይ ንዑስ ርዕስ ሥር የተካተቱበት ነው፡፡ መልዕክቶቹ አላህን የሚያስታውሱ፣ የሚያድሱ፣ የሚያነቃቁ ናቸው፡፡ ያላወቅነዉን ለማወቅ፤ የረሳነዉን ለማስታወስ ያግዙናል፡፡
አዘጋጅ – ሙሐመድ ሰዒድ
የገፅ ብዛት ፡ 206
የታተመበት ዓመት ፡ ግንቦት 2006
ከመጽሐፉ ፡
ሰዎች ከበሽታ፣ ከችግር፣ ከርሃብ፣ ከእርጅናና ከሞት ነፃ ለመውጣት ለዘመናት ሲናፍቁና ሲጥሩ ኖረዋል፡፡ ደስታና እርካታ ፍለጋም ሀገር ለሀገር ተንከራተዋል፡፡ ለዚህም ሲባል ብዙ ጉልበት፣ ሀብትና ጊዜ አባክነዋል፡፡ ሆኖም ዛሬም ድረስ ጠብ ያለላቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ማስቀደም የነበረባቸውን ነገር በመዘንጋታቸው ነው፡፡ መሰረቱን ትተው ቅርንጫፎች ላይ በማተኮራቸው ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወታቸው ላይ ብዙ ስላልሰሩ ነው፡፡ ስለሆነም ለተሟላ ሕይወትና ለአስተማማኝ የሕይወት ዋስትና ሁሉም ወደ አላህ (ሱ.ወ) ፊቱን ማዞር ያለበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ አላህን (ሱ.ወ) ይበልጥ ማወቅና ወደሱ መቅረብም ይገባናል፡፡ እሱን ማገልገልም የዕድሜ ልክ ሥራችን ልናደርገው ይገባል፡፡ ይህም ለሁለገብ ስኬት ያበቃናል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ

Category: