ሀምሳ ተረቶች ለልጆች

4.00 $

ይዘት ፡ ለልጆች አስተማሪ የሆኑ፣ በቀላል ቋንቋ የተፃፉ ሀምሳ የተለያዩ ተረቶች

ትርጉም – ዒማዱዲን ዙልፈቃር

የገጽ ብዛት – 229

ከመጽሐፉ ፡

በጎ አድራጊው ዝሆን ….

ለፍጡራን ሁሉ በጎ ማድረግን የሚወድ አንድ ዝሆን ነበር። ይህ ዝሆን፣ ከሌሎች እንስሳት ዘንድ “ደጉ ዝሆን “በመባል ይታወቃል።

ደጉ ዝሆን፣ ከዕለታት አንድ ቀን በመንገድ ላይ በመጓዝ ሳለ፣ ከጓደኛው ከጋሽ ዝንጀሮ ጋር ተገናኘ። ጋሽ ዝንጀሮ፣ ለደጉ ዝሆን ሠላምታ ካቀረበ በኋላ፣ “ምነው ሃሳብ ገባህ፣ ደህናም አይደለህ ወዳጄ?” ብሎ ጠየቀው።

ደጉ ዝሆን፡- “አዎን ወዳጄ፣ አንድ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ገጥሞኛል” አለ።

ጋሽ ዝንጀሮ፦ “ያንተ ነገር ይደንቀኛል፣ እንደልብህ የምትመገበው ያልተጓደለብህ ጠንካራ ዝሆን ሳለህ፣ ምን የሚያሳስብ ጉዳይ ገጠመህ?”

ደጉ ዝሆን፣ “እኔን ያሳሰበኝም ይኸውኮነው። ይህን ጉልበቴንና ጊዜዬን ለበጎ ተግባር ማዋል የምችልበትን መንገድ ነው የማስበው።”

ጋሽ ዝንጀሮ፡- “ቀኑን ሙሉ፣ ከዛፎች መካከልና ከወንዝ ዳርቻ ስትንሸራሸር፣ እንዲሁም በንፁህ አየር ስትናፈስና የፀሃይን ብርሃን እየኮመኮምህ መዋል ትችላለህኮ!”

ደጉ ዝሆን፡- “ቀኑን ሙሉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ማሳለፍ በጣም ያሰለቻል። የኔ ፍላጎት፣ በዙርያዬ ለሚኖሩ ፍጥረታት በሚጠቅም መልኩ ጊዜየንና ጉልበቴን ማዋል ነው። እባክህ ሌላ ሃሳብ ካለህ ጠቁመኝ?”

ጋሽ ዝንጀሮ፡- “እኔንጃ፣ ግን ምናልባት ከጫካው አቅራቢያ በሚገኘው መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ጥበበኛ ሰው አለ።”

ደጉ ዝሆን፡- “እንግዲያው ወደሱ ውሰደኛ፣ እንፍጠን!”

ደጉ ዝሆንና ጋሽ ዝንጀሮ፣ ከጠቢቡ ሰውዬ መኖሪያ ሲደርሱ፣ መግባት ይፈቅድላቸው እንደሆን በትህትና ጠየቁ። ጠቢቡ ሰውዬ እንዲገቡ ፈቀደላቸው።

“ሰላም ለዚህ ቤት!” አሉ።

“ግቡ ኖር ብያለሁ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ! ምን ልርዳችሁ?” በማለት ጠየቃቸው።

ደጉ ዝሆን፣ ጊዜውንና ጉልበቱን ለሌሎች ፍጥረታት በሚጠቅም ተግባር ላይ ለማዋል የሚችልበትን መላ እንዲጠቁመው ጠቢቡን ሰውዬ ጠየቀው።

….

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: