ሐላልን ፍለጋ

300.00 Br

ዝግጅት:  ሰዒድ ሺፈራው

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

በተለይ በዚህ ባለንበት ዓለም ተጨባጭ ኢስላማዊ ልብ ወለድ አፃፃፍ እስልምናን ለማስተማር ሌላኛው የዳዕዋ መንገድ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ መጽሐፍ በነጃሺ ሲታተም በዓይነቱ የመጀመርያው ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የካምፓስ ሕይወትን ዉሎ አዳርና የሐላል ጥምረት ፍለጋ ጉዞን ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉ ከእስልምና አስተምህሮ ባልወጣ መልኩ፣ አደብ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ፣ ቀጥተኛና ማራኪ በሆነ አገላለጽ የተዘጋጀ ነው፡፡ ወጣቶችም ሆነ ሌሎች ቢያነቡት ትምህርት ያገኙበታል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

ፈንጠር ብሎ ቆመና የቁርኣኑን ባለቤት ይጠብቅ ጀመር፡፡ በሀሳብ ግን ስምጥ ብሎ ሄዷል፡፡
‘‘የቁርኣን ክብር ይሄ ነው እንዴ? የአላህ ቃል ልቅና የት ገባ? እንደ ቀድሞው
ትውልድ ማክበር እንደሚገባን ምነው ዘነጋን? የቁርኣንን ተዓምር አቅላችንን ምን አሳጣው? ማማራችንስ መከበራችንስ በሱው አልነበረም እንዴ? ምን ነካን?’’
‘‘ዳዒዎቻችንስ ስለ ቁርኣን ክብር ጉዳይ በሰፊው ለምን አይሰብኩም? እነሱ ትኩረት በደንብ ካልሰጡት ቁርኣኑን በግራ እጁ ይዞ እግር ኳስ የሚጫወተውን ማን ይመልሰው?’’
ሰሐቦች ቁርኣንን ሲይዙ ለአላህ ካላቸው ፍቅር የተነሳ እያለቀሱ ‘‘ይህ የጌታችን ቃል ነው!’’ ይሉ ነበር የሚለውን ታሪክ ያነበበትን መጽሐፍ አስታወሰ፡፡
ወደ ቁርኣኑ አንዲት ሴት ስትሄድ ተመልክቶ ከሀሳቡ ተመልሶ እሱም ወደዚያው አመራ፡፡ …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

SKU: M103 Category: