24 ሰዓት በሙስሊም ህይወት

210.00 Br

አዘጋጅ፡ ሃሩን የሕያ

ትርጉም፡ ኢዘዲን አባፊጣ

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

መጽሐፉ ሙእሚን በ24(ሃያ አራት) ሰዓት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ሕይወት የሚያመለክት ነው፡፡ ቁርኣንን መሠረት ያደረገ የአንድ ሙስሊም ሕይወት ምን ይመስላል? ሙስሊም ከእንቅልፉ ከነቃበት ጊዜ አንስቶ ለመኝታ ጎኑን እስከሚያሳርፍ ድረስ እንዲሁም ሌሊቱን በምን መልኩ ማሳለፍ አለበት? የሚለውን መጽሐፉ ቁርኣንና ሐዲስን መሠረት አድርጐ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ የኢስላምን ሁለንተናዊነት በተፈኩር በተሞላ ጽሐፍ የሚያቀርብልን  ነው፡፡

 

ከመፅሐፉ በጥቂቱ፡

አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የሚረዱት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ጸሎት አድርገው ነው። በሌላ አነጋገር ሰዓታትን ከፋፍለው ጥቂቱን ለአምልኮ ቀሪውን ደግሞ ለሌሎች ጉዳዮቻቸው ማዋል እንዳለባቸው ያስባሉ። አላህ (ሱ.ወ)ወይም የትንሳኤ ቀንን የሚያስታውሱት ሲሰግዱ፣ ሲጾሙ፣ ሰደቃ (ምጽዋት) ሲሰጡ ወይም ሐጅ ለማድረግ ወደ መካ ሲጓዙ ብቻ ነው። ለነዚህ ተግባራት ከሚያውሉት አጭር ጊዜ ውጭ ያለውን አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ዘውታሪ ላልሆኑ ምድራዊ ፍላጎቶቻቸው ሲጨነቁና ሲጠበቡ ነው። በመሆኑም ሕይወት ማለት ለነርሱ ሌላውን በልጠው ለመገኘት የሚፍጨረጨሩበትና የማይቋጭ የሆነ ስኬት አልባ ትግል ነው። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ከሞላ ጎደል ከቁርኣናዊው የሕይወት መርህ ያፈነገጡ መሆናቸው ለዚህች ዓለም የራሳቸው የሆነ ዕይታና ትርጉም እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል። …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

SKU: M039 Category: