ኸሊፋ ዑሥማን (ረ.ዐ.)

90.00 Br

አዘጋጅ ፡ ዶ/ር መጂድ ዓሊካን

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ይዘት፡

የኢስላም ገናናነት ከሁለተኛው የሙስሊሞች ኸሊፋ ዑመር (ረ.ዐ) ሕልፈት በኋላም ቀጥሏል፡፡ ግና ከሦስተኛው ኸሊፋ ከዑሥማን ኢብን ዐፋን (ረ.ዐ) የኸሊፋነት ዘመን ማክተሚያ ጀምሮ የሙዓዊያ (ረ.ዐ) የበላይነት እስከ ተረጋገጠበት ጊዜ ድረስ (ከ36-60 ዓ.ሂ) የእርስ በርስ ግጭት ሰፍኖ ነበር፡፡ ይህ የዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ታሪክ እነዚህንና ሌሎች የኸሊፋውን ከኢስላም በፊትና በኋላ ፤የሐበሻ ሀገር ስደት፤ድሎቻቸው ን፤የኢራቅ እና የኢራን አስተዳደርንና ሌሎችም የኸሊፋውን ኢስላማዊ ተግባር ይተነትናል፡፡

 

ከመጽሐፉ፡

ሐድረት ዑመር ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ሙስሊሞች ከመካከላቸው ኸሊፋ እንዲመርጡና አዲስ ለተመረጠው ኸሊፋም ቃልኪዳን ይገቡ ዘንድ ስድስት ትላላቅና የተከበሩ ሶሐቦች ያሉበት አንድ ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡ ኮሚቴው ለረጅም ሰዓታት ስብሰባ ላይ ቢቀመጥም ከአንድ ዉሳኔ ላይ ለመድረስ ተሳነው፡፡ በዚህ ጊዜ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ አንድ ሰው ራሱን ከምርጫው እንዲያገልና በጉዳዩ ላይ ከዉሳ ለመድረስ እንዲቻል ሀሳብ አቀረቡ …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

SKU: T006 Category: