ረውደቱል አንዋር

450.00 Br

አዘጋጅ ፡ ሶፊዩረሕማን አልሙባረክፉሪ

ትርጉም ፡ የሕያ አባጀበል

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

መጽሐፉ በዓለም ደረጃ እጅግ ተነባቢ ከሆኑ ተወዳጅ መጽሐፎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በከፍተኛ ጥራትም ተዘጋጀ ነው፡፡ ፓኪስታናዊው የመጽሐፉ አዘጋጅ “ረሒቅ አል-መኽቱም” በተሠኘው መጽሐፋቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነትና እውቅና አላቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ የአላህ መልዕክተኛ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የህይወት ታሪክ ዉብ በሆነ አቀራረብና ቋንቋ የተሰናዳበት ነው፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

ዕድሜያቸው አርባ ሲሞላ ሰው ልጅ ሙሉ የሚሆንበትና አብዛኛው ነቢያት የተላኩበት ዕድሜ ላይ የነቢይነታቸው መገለጫዎችና የመልካም ዕድል ማብሰሪያዎች መገለጽ ጀመሩ፡፡ ጥሩ ህልም ያዩና ባዩት መሠረት በገሃድ ይከሠት ነበር፡፡ ብርሃን ያዩ፤ ድምጽ ይሰሙ ነበር፡፡ በአርባ አንደኛው ዓመታቸው በረመዷን ወር በሒራ ዋሻ ተቀምጠው አላህን በመገዛት ላይ እያሉ ጂብሪል ድንገት ነቢይነትንና ወሕይን ይዞ ከተፍ አለ፡፡ …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

SKU: T036 Category: