| Weight | 95 g |
|---|

ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ
120.00 Br
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዐሊ
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ ታላቅ የሱፊ ሸይኽና የሸሪዓ ሊቅ ናቸው፡፡ በዘመናዊ ዓለም አስተሳሰብና ምልከታም ያላቸው አሻራ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡ በመዝሀብ ሐንበሊ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ፈለግ የነበራቸው የጠለቀ ስልት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የዓለማችን ሀገራት ዘወትር እንዲታወሱ አብቅቷቸዋል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
መንፈሳዊ ትግል ብዙ ጥረት የሚፈልግ ክዋኔ ሲሆን በኢማን ተራራ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ለመገኘትና ድንቅ የተቅዋ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ጥረት ነው፡፡ ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ በዚህ መስክ ከፍ ያለ ጥናት አድርገዋል፡፡ ጥናታቸውን ለመረዳት ግን ጥቂት ሀሳቦች ስለሱፊዎችና ተሰዉፍ እናያለን፡፡
በዐቂዳ ትምህርት አላህን ብቻ ነጥሎ ማምለክ ግዴታ ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ከሺርክ ፍጹም የፀዳ መሰረት እንዲኖረው መታዘዙ የሃይማኖቱ ሕግ ነው፡፡ በአላህ መተማመንና ስለሁሉም ነገሮች ምንጭ ፈጣሪው ላይ አቋሙን መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህን ታላቅ የተቅዋ ፀዳል ለመጎናጸፍ ታዲያ ዚክር፣ ዒባዳህ፣ ዙህድ፣ ወዘተ.. እያልን በምንጠራቸው መንፈሳዊ ተግባራት ላይ መዘውተር ይኖርብናል፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




