| Weight | 176 g |
|---|

የፍልስጤም የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ
240.00 Br
አዘጋጅ ፡ ስለሺ ቱጂ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ከዛሬ ሰባ ምናምን ዓመት በፊት ፍልስጤም ነፃ ሀገር ነበረች፡፡ ኋላ ላይ በአንዳንድ ኃያላን ሀገራት ይሁንታና አስተባባሪነት አይሁዳውያን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተጠራርተው በጥገኝነት በፍልስጤም ምድር ሰፈሩ፡፡ በነርሱ እየታገዙና እየተስፋፉ በዚያው ምድር ኢስራኤል የምትባል አገር መሠረቱ፡፡ ቀስ በቀስም ጥንታዉያኑን ነባር ሕዝቦች ፍልስጤማዉያንን ክግዛታቸው ማፈናቀልና ከገዛ አገራቸው ማባረር ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ ፍልስጤማውያኑ በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር ሆነዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ ስደተኞች ሆነዋል፡፡ ግና ችግራቸው ዉስብስብ ቢሆንም ትግላቸዉን አላቆሙም፡፡ ይህ መጽሐፍ ይህንኑ ጉዳይ ሚዛናዊና መሳጭ በሆነ መልኩ ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
ሀገሩ የኛ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ የኛ ነበር፡፡ ከነርሱ ይልቅ እኛ በሀገሩ ዉስጥ ለረጅም ጊዜ ኖረናል፡፡ ከነርሱ በተሻለም ሀገሩ ላይ ሠርተናል ደክመናል፡፡ እኛ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ከምድሩ ጋር ያለን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግንኙነት ከአይሁዶች በእጅጉ ይልቃል፡፡ ስለዚህ እነርሱ ምድሩ ላይ አለን የሚሉት ጥንታዊ ታሪካዊ መብት ሀገሩን የመውሰድ መብት አይሠጣቸዉም፡፡ በተመሣሣይ መልኩ እኛም ዐረቦች በጥንታዊ ቤታችን ስፔን ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት መጠየቅ አንችልም፡፡ ስፔን በዐረቦች ለስምንት ምዕተ ዓመታት በተዳደረችበት ወቅት ገናና ከመሆኗም በተጨማሪ ለዘመናዊ የአውሮፓ ሥልጣኔ ፈርቀዳጅ ሆናለች፡፡ ….
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




