ሐላልና ሐራም ቁጥር 3

210.00 Br

አዘጋጅ፡ ፕ/ር ሸይኽ ዩሱፍ አልቀረዷዊ

ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ

 

ይዘት፡

በኢስላም በተፈቀዱ እና ባልተፈቀዱ ነገሮች ዙርያ የአንድን ሙስሊም ግላዊ ሕይወት የሚመለከቱ ጉዳዮች፣ አጠቃላይ ህይወት እምነቶችና ባህሎች፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች፣ ስለ ጋብቻና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች፣ ስለ ወሊድ ቁጥጥር፣ የተጋቢዎች የግንኙነት መብቶች፣ ስለ ወላጆችና ልጆች፣ ስለ መዝናኛ፣ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት እና ሌሎችም በጥልቀትና በምጥቀት የተዳሰሱበት ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

አዘጋጁ ዓለም አቀፍ እውቅ ሙስሊም ዳዒ ናቸው፡፡ በ1960 እ.ኤ.አ የጻፉት ይህ መጽሐፋቸው በዐረቡ ዓለም በሚሊዮን ቅጂዎች ተሽጧል፡፡ ከ28 ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ታትሟል፡፡ መጽሐፈ አንድ ሙስሊም ሐላልና ሐራም የሆኑ ነገሮችን ለይቶ እንዲያውቅ ይረዳል፡፡

 

ከመጽሐፉ ፡ የሰዉን ገንዘብ በግልጽም በስዉርም ያለአግባብ መንካት ሐራም እንደሆነው ሁሉ የራስ ገንዘብም ክብር አለው፡፡ ባለቤቱ እንዲያጠፋው እንዲያባክነው፣ እንደሻው እንዲበትነው አይፈቀድለትም፡፡ ምክንያቱም ማኅበረሰቡ ከግለሰቦች ገንዘብ የባለቤትነት ድርሻ አለው፡፡

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

SKU: F006 Category: