
የመልዕክተኛው ሰ.ዐ.ወ እንስት ባልደረቦች 100 የብልሓት ታሪኮች
140.00 Br
ቀደምት የየአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች -ወንዶቹም ሆኑ ሴቶች- ከተከበሩ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ሊኖሩና ሊተገበሩ የሚችሉ በርካታ ተምሣሌቶችን ትተውልን አልፈዋል። ከታሪካቸውና ከአስተምህሮአቸው የሚቀሰም ብዙ ትምህርት አለ፡፡ ሁሉም የብልህነት፣ የኢማን እና የንቃትና ግንዛቤ ውጤቶች ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ምንጭ ከሆኑት እጅግ ብልህ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሴት ባልደረቦችና የተወሰኑትን ከሌሎችም መካከል ታሪካቸውን ያስቃኘናል።
መጽሐፉ 100 ገፆች ያሉት ሲሆን በመንሱር ዐብዱልሐኪም ተዘጋጅቶ በወጣቱ ፀሀፊ ዐብዱረዛቅ ነጋሽ የተተረጎመ ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የእመት ኸዲጃን፣ ዓኢሻን፣ የሐፍሷን፣ የሰውዳን፣ የኡሙ ሰለማን፣ የዘይነብ ቢንት ጀሕሽን፣ የሶፍያን፣ የጁወይሪያን፣ ኡሙ ሐቢባን፣ የኡሙ አይመንን፣ የኡሙ መዕበድን፣ የአል-ኸንሳእን … ጨምሮ የመቶ ታላላቅ እንስቶች ብልህነት ይገኛል፡፡ ከሕይወታቸው ብዙ ብዙ ልምድ ይቀሰማል፣ ብዙ ቁምነገር ይገኛል፡፡
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ፡፡
*****




