| Weight | 250 g |
|---|

ተምሣሌት
335.00 Br
አዘጋጅ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር አደም
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ይዘት፡
መጽሐፉ ለየትኛውም የሰው ልጅ ተምሳሌት ሊሆኑ ስለሚችሉት ስለ ውዱ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ሕይወት ይዳስሳል፡፡ በአራት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን ከነቢይነት በፊት የነበረውን ሕይወታቸውን፤ ከነቢይነት በኋላ የነበረ ታሪካቸውን ፤ከስደት በኋላ የሠሯቸውን ሥራዎችና በመጨረሻም እስልምናን ለመከላከልና ለማስፋፋት ስላደረጓቸው ትግሎች ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ፡
ሰው በሕይወት ዘመኑ የሚያጋጥሙትን ክፍተቶች የነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት በማጥናት መሙላት ይኖርበታል። ምክንያቱም በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት ውስጥ የትላንቱ ታሪክ፣ የዛሬው ሕይወት፣ የነገው ተስፋ አለና። በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት ውስጥ የዚህን ዓለም መብራት፣ የመጭውን ዓለም መንገድ ይገኛል። የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት የማንነት ካርታ፣ የአእምሮ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ፣ ለሕይወት ውቅያኖስ መሻገሪያ መርከብ ነው። የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሲራ -ሕይወት የምትለመልምበትን ውሃ፣ የመዳንን ዘር፣ የስኬትን እርሾ የያዘ ነው። የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ለሰው ልጅ ሕይወት በሙሉ የተትረፈረፈ መረጃዎችን የሚያቀርብ ዓለም አቀፍና መለኮታዊ እውቅና ያለው የገበያ ማዕከል ነው::
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




