ኢቅረዕ

260.00 Br

ዝግጅት፡ ሙከሚል ከማል

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ ማኅበር

 

ይዘት፡

በይዘታቸው ትንሽ የሆኑ ነገር ግን ብዙኃኑን ማህበረሰብ ቁርዓንን ማንበብ ያስቻሉ ሁለት መጽሐፍት አሉ፡፡ እነዚህም ‹‹ቃዒደቱል ባግዳዲያ›› እና ‹‹ቃዒደቱል ኑራኒያ›› ይባላሉ፡፡የመጀመሪያው ከዐረብኛ ፊደላት ጀምሮ እስከ ‹‹ዓምመ›› ምእራፍ የያዘ ሲሆን ለበርካታ ዓመታት በሀገራችን ብዙዎች ይህን መጽሐፍ ተጠቅመው ቁርዓንን በመማር ለማንበብ በቅተዋል፡፡ ሁለተኛው ድግሞ በዐረብኛ አነባብ ላይ ብቻ ትኩረቱን በማድረግ ሰዎች በቀላሉ ቁርዓንን እንዲያነቡ ለማስቻል የቀረበ ስራ ነው፡፡ በውስጡ ምንም አይነት የቁርዓን ምእራፍ ያልያዘ ትኩረቱ ዐረብኛ እንዲነበብ ብቻ ያደረገ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ስራዎች ዐረብኛን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የዐረብኛ ህግጋትንም የሚያስተምሩ ስራዎች ናቸው፡፡ይህ ‹‹ኢቅረዕ›› የተሰኘው መጽሐፍ ለአማርኛ አንባቢዎች በቀላሉ ዐረብኛን ማንበብ እንዲችሉ ሁለቱንም ስራዎች በመጠቀም የተለያዩ ምሳሌዎችንና ማብራሪያዎችን ያካተተ ቁርዓንን ለመማር ለሚሹ ሰዎች ቀለል ባለ መልኩ  የቀረበ መጽሐፍ ነው፡፡

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

SKU: L014 Category: