| Weight | 309 g |
|---|
SOLD OUT

የታሪክ ንቅለ-ምልከታ
250.00 Br
አዘጋጅ፡ ፋኢዝ ሙሐመድ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ኢብራሒም አልጋዚ ሙሉ ስሙ ነው፡፡ ኢማሙ አሕመድ በሚለው ስሙ ይታወቃል፡፡ ሱማሌዎች ጉራይአ አቢሲኒያዎች ግራኝ ብለው ይጠሩታል፡፡ የሙስሊሙ ሊቃውንት ሰነዶች ይህን ስም አልተጠቀሙበትም፡፡ ‹‹ግራኝ›› የተባለው በግራ እጁ የሚጠቀም በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም በሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ እውን ኢማም አሕመድ ግራኝ ነበርን? ወደ ፊት ገጾች በማስረጃ እናየዋለን፡፡ በ1506 ሁበት የምትባል ቦታ ተወለደ፡፡ ሁበት ጋረሙለታ አከባቢ የሚገኝ ቦታ ነው የሚሉ ግምቶች ቢኖርም ሐረር እና ጅግጅጋ መካከል (ምን አልባት ባቢሌ አካባቢ) የሚለው ግምት የተሻለ ይመስላል፡፡
ይህ መጽሐፍ ከኢማም አሕመድ እስከ ዳግማዊ ምኒልክ ድረስ ያሉ የታሪክ ዕይታዎችንና የታሪክ ፍልስፍናን ኢማም አሕመድ ላይ የተነሱ ማጠልሸቶችንና እውነተኛ ማንነታቸውን፣ የተፈጠሩ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንና ማስተካከያዎችን የተለያዩ ጠንካራ መረጃዎችን በማቅረብ የሚዳሰስበት ጥናታዊ ስራ ነው፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************
Out of stock




