ኸዋሪጅ እና ሺዓ

190.00 Br

መነሻ ሐሳብ፡ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ አስ-ሶላቢ

ትርጉም፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ(ABX)

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/ተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘት፡

በእስልምና መንገድ ውስጥ ከተፈጠሩ ብዙ ቡድኖች ውስጥ ኸዋሪጅና ሺዓ ዋነኞቹ ቡድኖች ናቸው፡፡ ውስጣቸው የተለያዩ አይነቶች ሲሆኑ የተነሱበት መነሻ እሳቤዎችንም ይዘዋል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የሁለቱን ቡድኖች ምንነት መጠነኛ ቅኝትና ዳሰሳ ያደርጋል፡፡ ኸዋሪጆች ከመልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ዘመን ጀምሮ እስካለንበት ጊዜ ድረስ አጥፊ እንደሆነና ለብዙ ጥፋቶች መነሻ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዋናነት ይህ ቡድን ራሱን የብቸኛ የእስልምና ጠበቃ አድርጎ የመመልከት ባሕሪያትም አዳብሮ ይገኛል፡፡ በዘመናችንም በተለያየ ሁኔታ ራሱን በመለዋወጥ ሰዎች ዘንድ ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ ሌላኛው በመጽሐፉ ስለተጠቀሰው የሺዓ ቡድን ደግሞ አይነትና አስተሳሰቡም  የተለያዩ  ማጣቀሻዎችን በመጠቀም ስለምንነቱ ይገለጽበታል፡፡ መጽሐፉም ሰዎች እነዚህን ቡድኖች በዕውቀት በተደገፈ ሁኔታ እንዲያውቁትና በየጊዜው ከሚፈጠሩ ጽንፎችና አላዋቂነት እራሳቸውን እንዲከላከሉ ይጠቁማል፡፡

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

SKU: M135 Category: