| Weight | 1090 g |
|---|

ለዓለማት እዝነት (ሃርድ ከቨር)
1,500.00 Br
አዘጋጅ፡ ዶክተር ዐሊ ሙሐመድ አስ ሶልላቢ
ትርጉም፡ አሕመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ይዘት፡
ከኢስላም በፊት ከተፈጸሙ ታሪካዊ ክስተቶች ጀምሮ የመልእክተኛውን የሕይወት ታሪክ በሙሉ የዳሰሰው ለዓለማት እዝነት የተሰኘው መጽሐፍ በውስጡ ዳጎስ ያሉ ታሪኮችንና ከውስጡ የሚገኙትን አስተምህሮቶች ጨምሮ ይዟል፡፡ በቅድመ እስልምና የነበሩ ሥልጣኔዎች ምንነት ፤በቀደመው የአረብ ህዝቦች የዘር ግንድና ሥልጣኔያቸውን በስፋት ተዳሷል፡፡ የታላቁ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከልጅነት እስከ ነብይነት ፤የወህይ መውረድ፤የድብቅና ግልጽ የጥሪ ሂደት ካሳለፉት የዳዕዋ ሕይወት በርካታ ትምህርቶች ቀርበዋል፡፡መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) በዳዕዋ ሕይወታቸው የገጠማቸው ውጣ ውረድ መከራዎች ከመካ አጋሪዎች የተጋረጠባቸውን ፈተና፤ ወደ ሐበሻ ያደረጉትን ስደትና የገጠማቸውን ብርቱ የሐዘን አመት እያወሳ በዘመናችን ችግሮችን እንዴት እንደምንጋፈጥ ያስተምረናል፡፡በዳዕዋ ሕይወታቸው ያደረጉትን ትግል የተገቡላቸውን ቃልኪዳን፣ ወደ መካ ያደረጉትን ስደት፤ በመዲና ስለገነቡት መንግሥትና ያሳለፉትን ጣፋጭ ሕይወት ከነ ሙሉ ታሪኩና አስተምህሮቱ እንድንማርበት ተተርኮ ቀርቧል፡፡ ስለ መዲናው ህገመንግስት ፣ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዴት እንደኖሩ፣ ስለሙሃጂሮችና አንሳር ግንኙነቶች፣ እንዲሁም በዘመናቸው ስለ ተደረጉ ዘመቻዎች በልዩ አቀራር ይተነተንበታል፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************
Out of stock




