ኢስላማዊ እሴቶች

600.00 Br

አዘጋጅ፡ ሸይኽ ሐሰን አዩብ

ትርጉም፡ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ይዘት እና ስለመጽሐፉ ማብራሪያ

አዘጋጁ በኢስላማዊ መጽሐፍ ዝግጅት ታላላቅ ሥራዎቻቸው ከሚባለው አንዱ ነው ይህ መጽሐፍ፡፡ የኢስላማዊ ማኅበረሰብ ሥርዓታዊ መዋቅር ምን መምሰል እንዳለበት ባማረ አገላለጽ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳይ ነው፡፡ የኢስላማዊ የሥነ-ሕግ ብይኖችን የማስረጃ ጥቅሶችን ከቁርኣንና ሐዲስ ጋር በማጣቀስ የሙስሊም ምሁራን የሃሳብ ልዩነቶችን በማስማማት ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለማነጽ ጥረት አድርገዋል፡፡ መጽሐፉ የኢስላም ግላዊና ማኅበራዊ እሴቶችን በመዘርዘር ፋይዳቸዉንም አጉልቶ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

ኢስላማዊ  እሴቶችን  በጥልቀት የመዳሰሱ  ዓላማ የሙስሊሙን ሕሊና ከነበረበት ሰመመን ለማንቃት፤በራሱና በኢስላም ላይ መልካምን እንጅ መጥፎን አመለካከት እንዳያስቀምጥ፤ የስልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሰ ሙስሊም ማኅበረሰብ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በእርግጥ የሰው ልጅ ክቡር የሆነ ሕይወት ያለው፣ ለተሻለ ደረጃ የሚተጋ፣ በእውነተኛ ብርሃን የሚያንፀባርቅ፣  ክፋትን፣ ክህደትን፣ መጥፎነትን የማያውቅ፣ በንጹሕ ፍጡራን ላይ በተለይ እነዚህ ንጹሕ ፍጡራን ነፍሳት ቢሆኑም እንኳን ርኅራኄ ያለው፣ በራሱ (በነፍሱ) ኩሩ የሆነ፣ በእውነታ ላይ የማይተኛ፣ ለበደል እጅ የማይሰጥ፣ ከአላህ ሌላ ላለ ማንኛውም ነገር የማያጎነብስ ነው። …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

Out of stock

SKU: M061 Category: