| Weight | 73 g |
|---|

ሶላትን አደራ
120.00 Br
አዘጋጅ፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ(ABX)
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ትልቅ ቁምነገርና መልዕክት ይዛለች፤ ስለ ሶላት ምንነት፣ ዓላማና ሚስጢር ትዳስሳለች፣ ጥቅሟን እና ትሩፋቷን ታስቃኘናለች፣ አለመስገድ ከባድ ወንጀል እንደሆነ ታስታውሰናለች፣ ሶላት የማይሰግድ ሰው ስለሚጠብቀው ቅጣት ታወሳለች፣ ሙስሊም ሆኖ ያለ ሶላት ሰውነት ያለ አንገት ማለት ነው ትላለች፣ ሶላት ባትኖር ኖሮ ክፉኛ እንደምንጎዳ ታሳያለች፣ ሶላት ጀነት ነውና ኑ ወደ ጀነት ግቡ! ብላ ትጣራለች!!! መጽሐፏ በተለይ በሶላት ጉዳይ ችላ ለሚሉ አሊያም ለማይሰግዱ፣ ወይም ደግሞ ዓላማዋን በአግባቡ ላልተረዱት እና ለሌሎችም በስጦታ መልክ ብትበረከት እጅግ ጠቃሚ ናትና የመልዕክቷ ተቋዳሽና አድራሽ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ …
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
የሰው ልጅ በምድር ላይ የመፈጠሩ ዋና ዓላማ አላህን (ሱ.ወ.) ለማምለክ እንደሆነ እርግጥ ነው፡፡ አምልኮ ሲባልም ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ አላህን (ሱ.ወ.) ከምናመልክባቸው መንገዶች አንዱ ግዴታ የተደረጉብንን በቀን ዉስጥ አምስት ሶላቶችን በመወጣት ነው፡፡ በሶላት ለአላህ ባርነታችንን እንገልፃለን፡፡ ሰዎች ቃለ ተውሒድን ተቀብለው ወደ እስልምና የገቡ እንደሆነ ጥሪ የሚደረግላቸው ጠሃራ አድርገው ሶላት መስገድ እንዲጀምሩ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ታላቁን ሶሐባ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበልን ወደ የመን ሲልኩት እንዲህ ነበር ያሉት …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




