ተውበት ማድረግ እፈልጋለሁ ነገር ግን …

90.00 Br

ዝግጅት፡ ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊሕ አልሙነጂድ

ትርጉም፡ አወል ኸድር

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

በዲኑ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በአላህ መንገድ መጽናት ይፈልጋሉ፡፡ የራቁትም ቢሆኑ ተመልሰው እውነተኛ የአላህ ባርያ መሆን ይመኛሉ፡፡ እርግጥ ነው ከአላህ መንገድ የራቀ ሰው በዱንያ ጭንቀት ይዋጣል፡፡ በጥፋት ማዕበል ይዋዥቃል፡፡ ታድያ መቼም ይሁን መች ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ከተመለሰና እጁን ከሠጠ ዳግመኛ ፊቱን ወደ ጥፋት አያዙር እንጂ አላህ ሊምረው ይችላል፡፡ በመንገዱም ላይ ያፀናዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ተውበት በማድረግ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ኃጢኣትን አቅልሎ መመልከት ስለሚያስከትለው አደጋ፤ስለ ተውባና ምንነቱ፤ተውባ ለማድረግ እንቅፋት ስለሆኑ ነገሮችና ሌሎችም የተዳሰሱበት ነው፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

ተውበት ብታደርግም የበፊት ሕይወትህ ሲታወስህ “በርካታ ኃጢአቶችን እፈፅም ነበር። አሁን ወደ አላህ ምሕረት ተመልሼያለሁ። የሰራኋቸው ኃጢኣቶች ግን ዛሬም ትዝ እያሉኝ አዕምሮዬን ሰላም ነስተውታል። እንቅልፍም ሆነ እረፍት ያሳጡኛል። ከዚህ ዓይነት መረበሽ፣ ጭንቀትና መጥፎ ትውስታ እንዴት እገላገል ይሆን?” ለምትለው ተውበት አድራጊ ምላሼ “ይህ ስሜት ለኃጢአቶችሁ ከልብህ ተውበት ለማድረግህ ማስረጃ መሆኑን ያመለክታል” የሚል ነው። የዚህ ዓይነት አዋኪ ስሜት በመሠረቱ ጸጸት ነው። ፀፀት ደግሞ በራሱ ተውበት ነው። ያለፈ ሕይወትህን መቃኘት ያለብህ አላህ ይምረኛል በሚል  ተስፋ ይሁን። …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

 

 

 

 

SKU: M030 Category: